Logo for SMNE Solidarity Movement for a New EthiopiaContact usAmharic information
Humanity before Ethnicity

ደወል
ቁጥር 1 - 10


ደወል 1

ዝናውም፣ ክብሩም፣ ሃብቱም፣ ሁሉም ያልፋል። ጊዜም ከጥላችን ይልቅ ይበራል። ደጎች ላገራቸው፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለተተኪው ትውልድ መልካም ነገር አስቀምጠው ሲያልፉ በበጎ ሲታወሱ ይኖራሉ። የክፉ ታሪክና ልምድ ማጣቀሻ ከመሆንለአገርና ለወገን መልካም ስራ ሰርቶ ማለፍ ያኮራል።

ዓለምአምባገነኖችንተፀይፋለች።. . . የዓለምኃያላንአገሮችምአምባገነኖችንሥራችሁያውጣችሁእያሏቸውይገኛል።. . . የአምባገነኖችመጨረሻየቀንጉዳይካልሆነበስተቀርኢትዮጵያውስጥምእንደማይቀርበርግጠኛነትእንነግርዎታለን።

ስለዚህ ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንስጥ እንዲሁም ሁላችንም ነፃ ካልወጣን ማንም ነፃ አይሆንም በሚል መርሆ የተመሠረተውና በአገራችን ፍትሕ፣ ሰላም፣ አንድነትና ዕርቅ እንዲሰፍን ከሚታገለው ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄጋር እንዲቆሙ ይህንን የጥሪ ደወል እናሰማለን።


ደወል 2
. . . ይህንን እየራደ የሚገኝ ሥርዓት “እንቢ!” ያሉ  ወገኖቻችን የሚኖራቸውን ሞገስና ክብር፤ ከማይቀረው የኢህአዴግ ውድቀት በኋላ ተባባሪዎቹ ላይ ከሚደርስባቸው ውርደት ጋር በማነጻጸር ዛሬ ለእውነት እንቁም፡፡ ወደ ልባችን እንመለስ!! ለጥሪውም ምላሽ እንስጥ!!

. . . ከዘረኝነት ይልቅ ለሰብዓዊነት ክብርን ይስጡ፤ ለጥቅም ብለው የህወሃት/ኢህአዴግን አባልነት ፎርም በመሙላት ባርነትን አይቀበሉ። በኢህአዴግ ኦርኔል ላይ የውርደት ታሪክዎን በማስፈር በባርነት ለመገዛት፣ በቀጣዩ ትውልድ የመወንጀያና ወደ ወኅኒ የመውረጃ ሰነድ ለራስዎ አያኑሩ::


ደወል 3
. . . በአገራችንም እንተማመናለን። ምንም ይሁን ምን አገራችን የጋራችን ናት። እናታችንም ናት። አሁን ባሉበት ቦታ ለእርስዎም እናት ናት። ለሚከዱዋትም ለሚያምኑባትም ቆዳዋን ለሚገፏት፣ ለሚዘርፏት፣ ለከሃዲዎችም ኢትዮጵያ እናት ናት!! በክብር መኖር ለማይመኙ ባንዳዎች የመቀበሪያ፣ የመታሰሪያ፣የመዋረጃ ቦታም አላት። ከዚህ ግን ሁላችንንም ይሰውረን፡፡

…….‹‹በመንግሥት›› ደረጃ ስርዓት የፈረሰ፣ ህገወጥነት የነገሰ፣ ወሮበላነት እየተስፋፋ ለመሆኑ ለዓለም በቂ ማስረጃ ነው። የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝን በመደገፍ ወገኖቻቸውን እየረገጡ በሚገኙ ህሊና ቢሶች ላይ እየወረደ ያለው ጥላቻ ከፍቷል። እርስዎስ የዚህ ጥላቻ ሰለባ  መሆን ይፈልጋሉ? ወይስ ከብዙሃኑ ጋር ለፍትህ ይቆማሉ?


ደወል 4
. . . እስረኞችን እጃቸውን ሽቅብ ከጣራ ጋር በሠንሰለት በማሰር፣ ውስጥ እግራቸውን በመግረፍ፣ ወንዶቹን ብልታቸው ላይ ክብደት ያለው ዕቃ በማንጠልጠልና በማሰቃየት ታሳሪዎቹን አናዝዞ መረጃ ለማግኘት መሞከር የኢትዮጵያ እስርቤቶች አይነተኛ መገለጫ መሆኑ ዘገባው ማስረጃ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ይህ እንግዲህ እነ አቶ መለስ ደርግ ‹‹ሰው በላ ስርዓት›› ስለሆነ ‹‹ለሰፊው ሕዝብ ጥቅም›› ሲባል ያቋቋሙት ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት›› እያደረገ ካለው ኢሰብኣዊ ተግባር ጥቂቱ ነው፡፡

. . . ህዝብን በህዝብ ላይ በማነሣሣት በማህበራዊ ቀውስ ውስጥ የአገዛዝ ዕድሜውን ለማራዘም ከሚፈልግ ኢህአዴግ እንዲሁም ህዝብን በጥቅል በጠላትነት በመፈረጅ አንድ ቀን መውጪያ ቀዳዳ ሲያጣ  ኢንተርሐምዌ የጥፋት በትሩን ሊሰነዝር ከተዘጋጅ ህወሃት/ኢህአዴግ ጋር በአባልነት መቀጠል አዕምሮ የሌለው ሰው ውሳኔ ነው።


ደወል 5
. . . አንዱ ሲወድቅ እሱን አንስቶ ከፍ ባለ የሞራልና የዓላማ ልዕልና ትግሉን እየተቀባበሉ ወደፊት መሄድ ይጠይቃል፡፡ አስቀድሞ የነፃነትን ምንነትና የሚከፈለውን ዋጋ ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ አሁን የጀመርነው ትግል ግብታዊ ያልሆነ የተጠናና በስሜት የማይነዳ ሰላማዊ ትግል የአንድ ቅፅበት ግርግር  እንዳልሆነ ህወሃት/ኢህአዴግ ሊረዳ ይገባል።

. . . እርስዎ ወደውም ይሁን ተገደው የህወሃት/ኢህአዴግ መሣሪያ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ሆይ! የማንነትዎ መገለጫው፣ ክብርና ሞገስን የሚያጎናፅፍዎ ዛሬ እያገለገሉ ያሉትን ህወህት/ኢህአዴግን በመክዳት ለህዝባዊው ትግል አለኝታነትዎን መግለፅ ሲችሉ ብቻ ነው።


ደወል 6


. . . እርስዎ የኢህአዴግ አባል እንደመሆንዎ በፓርቲዎም ሆነ ባጠቃላይ በመዋቅሩ ውስጥ የተሳሳተ አሠራር ተመልክተው የማስተካከያ ሃሳብም ሆነ ተቃውሞ ቢያሰሙ በዚሁ ‹‹ፀረ ሽብርተኝነት›› ሕግ ተከስሰው ቅጣት መቀበልዎ የማይቀር መሆኑን ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ ምናልባትም የሚደርስብዎት ቅጣት እጅግ የከፋው እንደሚሆን ለመገመት አያዳግትም፡፡

. . . ትላንት ዛሬ አይሆንም - አልፏልና፡፡ ዛሬም ነገ አይሆንም - ገና አልመጣምና፡፡ የሰው ልጅ ማንነት የሚለካው ትላንት በፈጸመው ወይም ገና ወደፊት ሊፈጽም በሚያስበው አይደለም፡፡ አሁን፣ ዛሬ በእጁ ላይ ባለው ነው፡፡ ዛሬ በሚወስነው ውሳኔ እና በሚፈጽመው ተግባር የነገ ማንነቱን ያጸናበታል፡፡ ከሕዝብ ጋር የመቆሚያው ጊዜ ዛሬ - አሁን ነው፡፡ ዛሬን በማንአለብኝነት አሳልፎ ነገ ‹‹አድኑኝ›› ብሎ መማጸን የማይቻል ብቻ ሳይሆን የማይታሰብም ነው፡፡


ደወል 7
ንብ አውራውን ተከትሎ ሲነሳ፣ አዲስ ቦታ ሄዶ ሲከትም፣ ብቻውን የሚቀር የንብ ዓይነት አለ። እንዲህ ያለው ንብ እንደ ዋናዎቹ ንቦች መረጃ የለውም። ስራው ውሃ መቅዳትና ውሃ ማመላለስ ብቻ ነው። ይህ ንብ “ድንጉል” የሚባለው ነው። እንዲህ ተብሎለታል፡-
ንብ ሄደ፤ አውራው ሄደ፤ ያውም የወለደው፤
ከቤቱ የቀረው ድንጉል ድንጉሉ ነው፤ ቂጡ የከበደው፤

. . . ልብ ይበሉ  ህዝብ ያልተቀበለውና “በቃህ” ያለው መንግስት፣ ህዝብን በኑሮ፣ በእስር፣ በግርፋት፣ አስገድዶ በመድፈር፣ ንብረቱን በመቀማት፣ እኩል ባለማስተዳደር፣ መሬቱንና ድንበሩን በመቁረስ፣ የሚያሰቃይ አገዛዝ የህዝብ ቁጣ ይነድበታል። የህዝብ ቁጣ የነደደበት መንግስት መጨረሻውም ውድቀት በመሆኑ ሽሽት ሲጀምር ጭፍራውን አራግፎ ነው። ጭፍራውም ብቻውን ሲቀር ህዝብ እጅ ይወድቃል።


ደወል 8
. . . በልመና የአንድ ትውልድ ዘመን በላን። በገጠር፣ በከተማ ችግር የጠበሳቸው ህዝቦች ተብለን በችጋር፣ በድርቅና በረሃብ ትርጉም መከራከሪያ ሆነናል። ይህ ሁሉ አልበቃ ብሎን እስር፣ ግርፋት፣ አፈና፣ ስደት፣ ባይተዋርነት፣… ነግሶብናል። እስከመቼ በዚህ ይቀጥል? . . . ተቃዋሚ ባይኖርም እንኳ እያንዳንዱ ሥርዓት እንዳፈጣጠሩ መበስበሱና መሞቱ አይቀርም። አገርም፣ ተተኪ ትውልድም፣ የእርስዎም ልጆች ይቀጥላሉ። አቶ መለስም፣ ህወሃትም፣ ኢህአዴግም፣ ድቃይ ድርጅቶቹም፣ ሥልጣኑም፣ ሃብቱም፣ ክብሩም፣ ሁሉም ያልፋሉ።

. . . ኢትዮጵያ ነጻ ትወጣለች፤ ነጻ የምትወጣው ግን በሌላ ነጻ አውጪ ሳይሆን ነጻ አውጪውንም ጭምር ነጻ በሚያወጣው እውነት ነው፡፡


ደወል 9
. . . ከጋማ ከብቶች አስከሬን ላይ ከሰበሱት የደረቀ አጥንት ውስጥ መቅኔ ተገኝቶ መረቅ ሊጠጣ! አይ አፍሪካ፣ አይ መሪዎቻችን፣ እንዴት ይህንን ዘግናኝ ትዕይንት የተመለከተ ሰው ልቡ አይነካም? ከጥፋቱስ አይመለስም? ከዚህ በላይ ምን ልብ የሚያደማ ማስረጃ ለነፍሰ በላዎቹ ፖለቲከኞች ይቅረብ?….ለልጆቻቸው ምንም መግዛት ያቃታቸው አባቶች ልጆቻቸው ከተኙ በኋላ ሌሊት እየገቡ፣ ሌሊት እንደሚወጡ፣ በዚህም የተነሳ ልጆቻቸውን ማየት ያልቻሉ አባቶች እየበረከቱ መሆኑን የሰማነው መንግስት ከሌላት ሶማሊያ ሳይሆን ከአገራችን ኢትዮጵያ ነው።

. . . አቡክተው መጋገር፣ ጋግሮ መቁረስ፣ አቁላልተው መወጥወጥ፣ አርሶ መጉረስ፣ የሰማይ ያህል የራቃቸው ወገኖች ሌማታቸው ደረቋል፤ ቦሃቃቸው አድርቷል። በደጉ ጊዜ የሰበሰቡዋቸው የማብሰያ ቁሳቁሶች እንደ ቅርስ እቃ ካገልግሎት ውጭ የሆኑባቸው ሚሊዮኖች ጠኔ ጠንቶባቸው ልጆቻቸውን ወደጎዳና በመላክ ስጋቸውን እንዲሸጡ መግፋት ያባትነትና የናትነት ወግ ሆኖባቸዋል።


ደወል 10
መጀመሪያ ወደ ኮሙኒስቶች መጡ፤ ኮሙኒስት ስላልነበርኩ ምንም አልተናገርኩም፤ ቀጥሎም በሠራተኛ ማኅበር አባላት ላይ ዘመቱ፤ የሠራተኛ ማኅበር አባል ባለመሆኔ ምንም አልተናገርኩም፤ ከዚያም በአይሁዶች ላይ ተነሱባቸው፤ አይሁድ ስላልነበርኩ ምንም አልተናገርኩም፤ በመጨረሻ ላይ ግን እኔው ላይ መጡብኝ፤ የዚያን ጊዜ ግን ስለእኔ የሚሟገት ማንም አልተረፈም ነበር፡፡”

. . . ታዲያ እርስዎስ “ለውጥ፣ ዕድገት፣ ሕዳሴ ይመጣል” በማለት እየሞተ ያለውን የህወሃት/ኢህአዴግ ሥርዓት ደጋፊና አባል ሆነው እስከመቼ ይቀጥላሉ? የህወሃት ጥቃት በጋዜጠኞች፣ በሠራተኛ ማኅበራት፣ በሰላማዊ ዜጎች፣ ወዘተ ላይ ሲሰነዘር ቆይቷል፡፡ እርስዎም እስካሁን “እኔን አይመለከተኝም” ሲሉ ሰንብተዋል፡፡ ቀጣዩ በትር የሚሰነዘረው ግን በእርስዎ ላይ ነው፡፡ ታዲያ ያኔ ምን ይሆን መልስዎ? ማንስ እንዲቆምልዎት ይጠብቃሉ?


              return to top